ማርቆስ 6:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 እሱም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ።+ ከዚያም ዳቦውን ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ሁለቱን ዓሣም ለሁሉም አከፋፈለ። ማርቆስ 8:6-8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ። ከዚያም ሰባቱን ዳቦ ይዞ አምላክን አመሰገነ፤ ቆርሶም እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነሱም ለሕዝቡ አደሉ።+ 7 ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎችም ነበሯቸው፤ እነዚህንም ከባረከ በኋላ እንዲያድሉ ነገራቸው። 8 ሕዝቡም በልቶ ጠገበ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ ዮሐንስ 2:7-9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ኢየሱስም “ጋኖቹን ውኃ ሙሏቸው” አላቸው። እነሱም እስከ አፋቸው ድረስ ሞሏቸው። 8 ከዚያም “አሁን ቀድታችሁ ለድግሱ አሳዳሪ ስጡት” አላቸው። እነሱም ወስደው ሰጡት። 9 የድግሱ አሳዳሪም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውኃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደመጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ
41 እሱም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ።+ ከዚያም ዳቦውን ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ሁለቱን ዓሣም ለሁሉም አከፋፈለ።
6 እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ። ከዚያም ሰባቱን ዳቦ ይዞ አምላክን አመሰገነ፤ ቆርሶም እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነሱም ለሕዝቡ አደሉ።+ 7 ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎችም ነበሯቸው፤ እነዚህንም ከባረከ በኋላ እንዲያድሉ ነገራቸው። 8 ሕዝቡም በልቶ ጠገበ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+
7 ኢየሱስም “ጋኖቹን ውኃ ሙሏቸው” አላቸው። እነሱም እስከ አፋቸው ድረስ ሞሏቸው። 8 ከዚያም “አሁን ቀድታችሁ ለድግሱ አሳዳሪ ስጡት” አላቸው። እነሱም ወስደው ሰጡት። 9 የድግሱ አሳዳሪም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውኃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደመጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ