2 ዜና መዋዕል 28:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በተጨማሪም አካዝ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ዕቃዎች ሰበሰበ፤ ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ቤት ዕቃዎች ሰባበረ፤+ የይሖዋን ቤት በሮች ዘጋ፤+ በኢየሩሳሌምም በየመንገዱ ማዕዘን ላይ መሠዊያዎችን ለራሱ ሠራ። 25 በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት የሚጨስ መሥዋዕት የሚቀርቡባቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠራ፤+ በዚህም የአባቶቹን አምላክ ይሖዋን አስቆጣ። 2 ዜና መዋዕል 33:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ 55 ዓመት ገዛ።+ 2 ዜና መዋዕል 33:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በተጨማሪም ይሖዋ “ኢየሩሳሌም ለዘላለም በስሜ ትጠራለች”+ ብሎ በተናገረለት በይሖዋ ቤት ውስጥ መሠዊያዎችን ሠራ።+
24 በተጨማሪም አካዝ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ዕቃዎች ሰበሰበ፤ ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ቤት ዕቃዎች ሰባበረ፤+ የይሖዋን ቤት በሮች ዘጋ፤+ በኢየሩሳሌምም በየመንገዱ ማዕዘን ላይ መሠዊያዎችን ለራሱ ሠራ። 25 በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት የሚጨስ መሥዋዕት የሚቀርቡባቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠራ፤+ በዚህም የአባቶቹን አምላክ ይሖዋን አስቆጣ።