የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 26:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 የዳቦ እጥረት እንዲከሰትባችሁ+ በማደርግበት ጊዜ* አሥር ሴቶች በአንድ ምድጃ ብቻ ዳቦ ይጋግሩላችኋል፤ ዳቦውንም እየመዘኑ ያከፋፍሏችኋል፤+ እናንተም ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም።+

  • ዘዳግም 28:53
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 53  ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በአንተ ላይ ከሚያደርሰው ሥቃይ የተነሳ አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን የሆድህን ፍሬ ይኸውም የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።+

  • ኤርምያስ 37:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 በመሆኑም ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ እንዲታሰር አዘዘ፤ ዳቦ ከከተማዋ እስኪጠፋ ድረስም+ ከዳቦ ጋጋሪዎች ጎዳና በየዕለቱ አንድ አንድ ዳቦ ይሰጠው ነበር።+ ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ ተቀመጠ።

  • ኤርምያስ 38:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታል።+ ለከለዳውያን እጁን የሚሰጥ* ግን ይተርፋል፤ ሕይወቱ * እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤* በሕይወትም ይኖራል።’+

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ከውኃ ጥም የተነሳ፣ የሚጠባው ሕፃን ምላስ ከላንቃው ጋር ይጣበቃል።

      ልጆች ምግብ ይለምናሉ፤+ አንዳች ነገር የሚሰጣቸው ግን የለም።+

  • ሕዝቅኤል 4:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኢየሩሳሌም የምግብ አቅርቦቱ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ እነሱም እየተመጠነ የሚሰጣቸውን ዳቦ በሚዛን እየለኩ በከፍተኛ ጭንቀት ይበላሉ፤+ እየተመጠነ የሚሰጣቸውንም ውኃ እየለኩ በስጋት ይጠጣሉ።+

  • ሕዝቅኤል 5:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “‘“ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤+ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ፤ ከአንቺ የቀሩትንም በሙሉ በየአቅጣጫው* እበትናቸዋለሁ።”’+

  • ሕዝቅኤል 5:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር* ይሞታል ወይም በመካከልሽ በረሃብ ያልቃል። ሌላ አንድ ሦስተኛ ደግሞ በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል።+ የመጨረሻውን አንድ ሦስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው* እበትነዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ