-
1 ነገሥት 7:16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 እንዲሁም በዓምዶቹ አናት ላይ የሚሆኑ ሁለት የዓምድ ራሶችን ከመዳብ ሠራ። የአንደኛው የዓምድ ራስ ቁመት አምስት ክንድ የሌላኛው የዓምድ ራስ ቁመትም አምስት ክንድ ነበር።
-
-
1 ነገሥት 7:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የዓምድ ራሶቹ በሁለቱ ዓምዶች ላይ፣ ልክ ከመረብ ሥራው ቀጥሎ ካለው ከሆዱ በላይ ነበሩ፤ በእያንዳንዱ የዓምድ ራስ ዙሪያ 200 ሮማኖች በረድፍ ተደርድረው ነበር።+
-
-
ኤርምያስ 52:21-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ዓምዶቹ እያንዳንዳቸው 18 ክንድ* ቁመት ነበራቸው፤ የዙሪያቸው መጠን በመለኪያ ገመድ 12 ክንድ፣+ ውፍረታቸውም አራት ጣት* ሲሆን ውስጣቸው ክፍት ነበር። 22 በዓምዱም አናት ላይ ያለው ጌጥ ከመዳብ የተሠራ ነበር፤ የአንዱ ጌጥ ርዝማኔ አምስት ክንድ+ ሲሆን በዙሪያው ያሉት ሮማኖችና መረቡ በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። ሁለተኛው ዓምድ፣ ሮማኖቹን ጨምሮ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነበር። 23 በጎኖቹ ላይ* 96 ሮማኖች የነበሩ ሲሆን በመረቡ ዙሪያ ያሉት ሮማኖች በጠቅላላ 100 ነበሩ።+
-