የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 40:7-9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 በኋላም ከሰዎቻቸው ጋር በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደሾመው እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት ባልተወሰዱትና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት ድሆች የሆኑ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ።+ 8 ስለሆነም በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣+ የቃሬሃ ልጆች የሆኑት ዮሃናን+ እና ዮናታን፣ የታንሁመት ልጅ ሰራያህ፣ የነጦፋዊው የኤፋይ ልጆችና የማአካታዊው ልጅ የዛንያህ+ እንዲሁም አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች ናቸው። 9 የሳፋን ልጅ፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነሱና አብረዋቸው ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ብሎ ማለላቸው፦ “ከለዳውያንን ማገልገል አያስፈራችሁ። በምድሪቱ ላይ ኑሩ፤ የባቢሎንንም ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ