3 ከዚህም በላይ ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር+ የተነሳ ለቅዱሱ ቤት አስቀድሞ ካዘጋጀሁት በተጨማሪ የግል ሀብቴ+ የሆነውን ወርቅና ብርም ለአምላኬ ቤት እሰጣለሁ፤ 4 ከዚህም ሌላ የቤቶቹን ግድግዳ ለመለበጥ 3,000 ታላንት የኦፊር ወርቅና+ 7,000 ታላንት የተጣራ ብር፣ 5 በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ለሚሠሩትም ሥራ ሁሉ የሚያስፈልገውን እሰጣለሁ። ታዲያ ዛሬ ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጁ ይዞ ለመቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ማን ነው?”+