ዘፍጥረት 29:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ሊያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይህ የሆነው ይሖዋ መከራዬን ስላየልኝ ነው፤+ ከእንግዲህ ባሌ ይወደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል*+ አለችው። ዘፍጥረት 49:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “ሮቤል፣+ አንተ የበኩር ልጄ ነህ፤+ ኃይሌና የብርታቴ የመጀመሪያ ፍሬ ነህ፤ የላቀ ክብርና የላቀ ኃይል ነበረህ። 4 እንደሚናወጥ ውኃ ስለምትዋልል የበላይ አትሆንም፤ ምክንያቱም አባትህ አልጋ ላይ ወጥተሃል።+ በዚያን ወቅት መኝታዬን አርክሰሃል። በእርግጥም አልጋዬ ላይ ወጥቷል!
3 “ሮቤል፣+ አንተ የበኩር ልጄ ነህ፤+ ኃይሌና የብርታቴ የመጀመሪያ ፍሬ ነህ፤ የላቀ ክብርና የላቀ ኃይል ነበረህ። 4 እንደሚናወጥ ውኃ ስለምትዋልል የበላይ አትሆንም፤ ምክንያቱም አባትህ አልጋ ላይ ወጥተሃል።+ በዚያን ወቅት መኝታዬን አርክሰሃል። በእርግጥም አልጋዬ ላይ ወጥቷል!