11 ካህናቱ ከቅዱሱ ስፍራ በወጡ ጊዜ (በዚያ የተገኙት ካህናት ሁሉ ከየትኛውም ምድብ+ ይሁኑ ራሳቸውን ቀድሰው ነበር)፣+ 12 ከአሳፍ፣+ ከሄማን፣+ ከየዱቱን+ እንዲሁም ከወንዶች ልጆቻቸውና ከወንድሞቻቸው ወገን የሆኑት ሌዋውያን ዘማሪዎች+ ሁሉ ጥራት ያለው ልብስ ለብሰውና ሲምባል፣ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይዘው ነበር፤ ከመሠዊያው በስተ ምሥራቅ ቆመው የነበረ ሲሆን ከእነሱም ጋር መለከት የሚነፉ 120 ካህናት ነበሩ።+