18 “የሞረሸቱ ሚክያስ+ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤
ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+
የቤቱም ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ይሆናል።”’+
19 “ታዲያ በዚያ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉት? ይልቁንም ይሖዋን ፈርቶ፣ ይሖዋ እንዲራራለት አልተማጸነም? ከዚህስ የተነሳ ይሖዋ በእነሱ ላይ ሊያመጣ አስቦት የነበረውን ጥፋት አልተወውም?+ እኛ ግን በራሳችን ላይ ጥፋት እየጋበዝን ነው።