-
ዘዳግም 7:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 አንተም አምላክህ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ፣ ታማኝ አምላክ እንዲሁም ለሚወዱትና ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ መሆኑን በሚገባ ታውቃለህ።+
-
-
1 ነገሥት 8:23-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ+ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር+ የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር የለም።+ 24 ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቀሃል። በገዛ አፍህ ቃል ገባህ፤ ዛሬ ደግሞ በራስህ እጅ ፈጸምከው።+ 25 አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ ‘አንተ በፊቴ እንደተመላለስከው ሁሉ ልጆችህም በጥንቃቄ በፊቴ ከተመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከፊቴ ፈጽሞ አይታጣም’ በማለት ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቅ።+ 26 አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ እባክህ ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም።
-