የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 12:48
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 48 በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለና ለይሖዋ ፋሲካን ማክበር ከፈለገ የእሱ የሆኑት ወንዶች ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያ በኋላ በዓሉን ለማክበር መቅረብ ይችላል፤ እሱም እንደ አገሩ ተወላጅ ይሆናል። ነገር ግን ማንኛውም ያልተገረዘ ሰው ከፋሲካው ምግብ መብላት አይችልም።+

  • ሩት 1:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል።+

  • 2 ነገሥት 5:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከዚያ በኋላ አጃቢዎቹን አስከትሎ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ተመለሰ፤+ በፊቱም ቆሞ “በእስራኤል እንጂ በምድር ላይ በሌላ በየትኛውም ቦታ አምላክ እንደሌለ አሁን አውቄአለሁ።+ እባክህ ከአገልጋይህ ስጦታ* ተቀበል” አለው።

  • ኢሳይያስ 56:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድና

      የእሱ አገልጋዮች ለመሆን

      ከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+

      ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣

      ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣

       7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+

      በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ።

      የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ።

      ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+

  • የሐዋርያት ሥራ 8:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ* ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም* አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ