-
1 ዜና መዋዕል 22:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ከዚያም ዳዊት “የእውነተኛው አምላክ የይሖዋ ቤት በዚህ ይሆናል፤ ለእስራኤል የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያም በዚሁ ይቆማል” አለ።+
-
-
2 ዜና መዋዕል 15:8, 9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 አሳ ይህን ቃልና ነቢዩ ኦዴድ የተናገረውን ትንቢት ሲሰማ ተበረታታ፤ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶችም ከይሁዳና ከቢንያም ምድር ሁሉ እንዲሁም በተራራማው የኤፍሬም ክልል ከያዛቸው ከተሞች አስወገደ፤+ ከይሖዋ ቤት በረንዳ ፊት ለፊት የነበረውን የይሖዋን መሠዊያም አደሰ።+ 9 እሱም ይሁዳንና ቢንያምን ሁሉ እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነሱ ጋር የተቀመጡትን የባዕድ አገር ሰዎች ሰበሰበ፤+ አምላኩ ይሖዋ ከእሱ ጋር እንደሆነ ባዩ ጊዜ በርካታ የባዕድ አገር ሰዎች እስራኤልን ትተው ወደ እሱ መጥተው ነበር።
-