34 ይሁንና አንድ ሰው በነሲብ ቀስቱን ሲያስወነጭፍ የእስራኤልን ንጉሥ የጥሩሩ መጋጠሚያ ላይ ወጋው። ስለሆነም ንጉሡ ሠረገላ ነጂውን “ክፉኛ ስለቆሰልኩ ሠረገላውን አዙረህ ከጦርነቱ ይዘኸኝ ውጣ” አለው።+ 35 ያን ቀን ሙሉ የተፋፋመ ውጊያ ተካሄደ፤ ንጉሡንም ሠረገላው ውስጥ እንዳለ ፊቱን ወደ ሶርያውያን አዙረው ደግፈው አቆሙት። ከቁስሉ የሚወጣውም ደም በጦር ሠረገላው ውስጥ ይፈስ ነበር፤ አመሻሹም ላይ ሞተ።+