-
ዘኁልቁ 20:17, 18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 እናም አሁን እባክህ በምድርህ እንለፍ። በየትኛውም እርሻ ወይም በየትኛውም የወይን ቦታ አቋርጠን አንሄድም፤ ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር ሳንል በንጉሡ መንገድ እንሄዳለን።’”+
18 ኤዶም ግን “ክልላችንን አቋርጠህ ማለፍ አትችልም። እንዲህ ካደረግክ ወጥቼ በሰይፍ እገጥምሃለሁ” አለው።
-
-
ዘዳግም 2:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ከሞዓብ ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ ስለማልሰጥህ ከእሱ ጋር አትጣላ ወይም ጦርነት አትግጠም፤ ምክንያቱም ኤርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።+
-
-
ዘዳግም 2:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ወደ አሞናውያን በቀረብክ ጊዜ እነሱን አታስቆጣቸው ወይም አትተናኮላቸው፤ ምክንያቱም ምድሪቱን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ስለሰጠኋቸው ከአሞን ልጆች ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ አልሰጥህም።+
-