የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 12:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ኢዮዓስ ካህናቱን እንዲህ አላቸው፦ “ቅዱስ መባ+ ሆኖ ወደ ይሖዋ ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ ማለትም እያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅበትን ገንዘብ፣+ አንድ ሰው* እንዲከፍል የተተመነበትን ገንዘብና እያንዳንዱ ሰው ልቡ አነሳስቶት ወደ ይሖዋ ቤት የሚያመጣውን ገንዘብ በሙሉ ውሰዱ።+ 5 ካህናቱ በግል ቀርበው ገንዘቡን ከለጋሾቻቸው* ላይ መቀበል ይችላሉ፤ ከዚያም በቤቱ ውስጥ የፈረሰውን* ሁሉ ለመጠገን ይጠቀሙበት።”+

  • 2 ዜና መዋዕል 29:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 ሕዝቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ አቢያህ ትባል ነበር፤ እሷም የዘካርያስ ልጅ ነበረች።+

  • 2 ዜና መዋዕል 29:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 መግዛት በጀመረ በመጀመሪያው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር የይሖዋን ቤት በሮች ከፈተ፤ አደሳቸውም።+

  • 2 ዜና መዋዕል 34:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 እነሱም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ መጥተው ወደ አምላክ ቤት የመጣውን ገንዘብ አስረከቡት፤ ገንዘቡም በር ጠባቂዎች ሆነው የሚያገለግሉት ሌዋውያን ከምናሴ፣ ከኤፍሬም፣ ከቀረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ+ እንዲሁም ከይሁዳ፣ ከቢንያምና ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የሰበሰቡት ነበር። 10 ከዚያም በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሠራተኞች ገንዘቡን ሰጧቸው። በይሖዋ ቤት የሚሠሩት ሠራተኞች ደግሞ ቤቱን ለመጠገንና ለማደስ አዋሉት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ