-
2 ነገሥት 15:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ይሖዋ ንጉሡን ቀሰፈው፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ የሥጋ ደዌ+ በሽተኛ ሆኖ ኖረ፤ በአንድ የተለየ ቤትም ውስጥ ተገልሎ ተቀመጠ፤+ በዚህ ጊዜ የንጉሡ ልጅ ኢዮዓታም+ በቤቱ* ላይ ተሹሞ በምድሪቱ በሚኖረው ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።+ 6 የቀረው የአዛርያስ ታሪክ፣+ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 7 በመጨረሻም አዛርያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ እነሱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮዓታም ነገሠ።
-