2 ነገሥት 15:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሄ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ ወረራ በማካሄድ ኢዮንን፣ አቤልቤትማዓካን፣+ ያኖአህን፣ ቃዴሽን፣+ ሃጾርን፣ ጊልያድን+ እንዲሁም ገሊላን ይኸውም መላውን የንፍታሌም+ ምድር ያዘ፤ ነዋሪዎቹንም በግዞት ወደ አሦር ወሰደ።+ 2 ነገሥት 16:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በመሆኑም አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር+ መልእክተኞች ልኮ “እኔ አገልጋይህና ልጅህ ነኝ። መጥተህ በእኔ ላይ ጥቃት ከሚሰነዝሩት ከሶርያ ንጉሥ እጅና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” አለው። 8 ከዚያም አካዝ በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች ያለውን ብርና ወርቅ በመውሰድ ለአሦር ንጉሥ ጉቦ ሰጠ።+ 1 ዜና መዋዕል 5:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 በመሆኑም የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፑልን መንፈስ አነሳሳ+ (የአሦርን ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን+ መንፈስ ማለት ነው)፤ እሱም ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴ ነገድ እኩሌታን በግዞት ወደ ሃላህ፣ ወደ ሃቦር፣ ወደ ሃራ እና ወደ ጎዛን+ ወንዝ ወሰዳቸው፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይገኛሉ።
29 በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሄ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ ወረራ በማካሄድ ኢዮንን፣ አቤልቤትማዓካን፣+ ያኖአህን፣ ቃዴሽን፣+ ሃጾርን፣ ጊልያድን+ እንዲሁም ገሊላን ይኸውም መላውን የንፍታሌም+ ምድር ያዘ፤ ነዋሪዎቹንም በግዞት ወደ አሦር ወሰደ።+
7 በመሆኑም አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር+ መልእክተኞች ልኮ “እኔ አገልጋይህና ልጅህ ነኝ። መጥተህ በእኔ ላይ ጥቃት ከሚሰነዝሩት ከሶርያ ንጉሥ እጅና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” አለው። 8 ከዚያም አካዝ በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች ያለውን ብርና ወርቅ በመውሰድ ለአሦር ንጉሥ ጉቦ ሰጠ።+
26 በመሆኑም የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፑልን መንፈስ አነሳሳ+ (የአሦርን ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን+ መንፈስ ማለት ነው)፤ እሱም ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴ ነገድ እኩሌታን በግዞት ወደ ሃላህ፣ ወደ ሃቦር፣ ወደ ሃራ እና ወደ ጎዛን+ ወንዝ ወሰዳቸው፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይገኛሉ።