-
2 ነገሥት 16:10-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ከዚያም ንጉሥ አካዝ የአሦርን ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶርን ለማግኘት ወደ ደማስቆ ሄደ። በደማስቆ የነበረውን መሠዊያ ባየ ጊዜ ንጉሥ አካዝ የመሠዊያውን ንድፍና እንዴት እንደተሠራ የሚያሳይ መግለጫ ለካህኑ ለዑሪያህ ላከለት።+ 11 ካህኑ ዑሪያህ+ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት መመሪያ መሠረት መሠዊያውን ሠራ።+ ካህኑ ዑሪያህ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ ከመመለሱ በፊት ሠርቶ አጠናቀቀ። 12 ንጉሡ ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ መሠዊያውን አየው፤ ወደ መሠዊያውም ቀርቦ በላዩ ላይ መባ አቀረበ።+ 13 እንዲሁም በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መባውና የእህል መባው እንዲጨስ አደረገ፤ የመጠጥ መባውንም አፈሰሰ፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ደም ረጨ።
-