17 “አንድ ሰው ይሖዋ እንዳይደረጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ኃጢአት ቢሠራ፣ እንዲህ ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ በደለኛ ይሆናል፤ በሠራውም ጥፋት ይጠየቅበታል።+ 18 የበደል መባ እንዲሆንም የተተመነለትን ዋጋ ያህል የሚያወጣ እንከን የሌለበት አውራ በግ ከመንጋው መካከል ወስዶ ለካህኑ ያምጣ።+ ከዚያም ካህኑ፣ ሰውየው ባለማወቅ ለፈጸመው ስህተት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።