6 በተጨማሪም በአሐሽዌሮስ የግዛት ዘመን መጀመሪያ ላይ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ በጽሑፍ ክስ መሠረቱባቸው። 7 ከዚህም ሌላ በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፣ ሚትረዳት፣ ታብኤልና የቀሩት ግብረ አበሮቹ ለንጉሥ አርጤክስስ ደብዳቤ ጻፉ፤ ደብዳቤውንም ወደ አረማይክ ቋንቋ+ ተርጉመው በአረማይክ ፊደል ጻፉት።
8 ዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ረሁም እና ጸሐፊው ሺምሻይ ኢየሩሳሌምን በመክሰስ ለንጉሥ አርጤክስስ የሚከተለውን ደብዳቤ ጻፉ፦