19 ሆሮናዊው ሳንባላጥና አሞናዊው+ ባለሥልጣን ጦብያ+ እንዲሁም የዓረብ+ ተወላጅ የሆነው ጌሼም ይህን ሲሰሙ ያፌዙብንና+ በንቀት ዓይን ይመለከቱን ጀመር፤ እንዲህም አሉን፦ “ምን እያደረጋችሁ ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ነው?”+ 20 እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩላቸው፦ “ሥራችንን የሚያሳካልን የሰማይ አምላክ ነው፤+ እኛ አገልጋዮቹም ተነስተን እንገነባለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ዓይነት ድርሻም ሆነ መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም።”+