-
ነህምያ 6:10-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ከዚያም የመሄጣቤል ልጅ ወደሆነው ወደ ደላያህ ልጅ ወደ ሸማያህ ቤት ሄድኩ፤ እሱም ቤቱ ውስጥ ነበር። እንዲህም አለኝ፦ “ሊገድሉህ ስለሚመጡ በእውነተኛው አምላክ ቤት ይኸውም ቤተ መቅደሱ ውስጥ መቼ እንደምንገናኝ እንቀጣጠር፤ የቤተ መቅደሱንም በሮች እንዝጋ። አንተን ለመግደል በሌሊት ይመጣሉ።” 11 እኔ ግን “እንደ እኔ ያለ ሰው መሸሽ ይገባዋል? ደግሞስ እንደ እኔ ያለ ሰው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ገብቶ በሕይወት ሊኖር ይችላል?+ በፍጹም አልገባም!” አልኩት። 12 ከዚያም ይህን ሰው አምላክ እንዳላከው ከዚህ ይልቅ ጦብያና ሳንባላጥ+ በእኔ ላይ ይህን ትንቢት እንዲናገር እንደቀጠሩት ተገነዘብኩ።
-