7 መርዶክዮስም ያጋጠመውን ነገር ሁሉ ነገረው፤ እንዲሁም ሃማ አይሁዳውያንን ለማጥፋት+ ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማስገባት ቃል ስለገባው ገንዘብ መጠን ነገረው።+ 8 በተጨማሪም እነሱን ለማጥፋት በሹሻን+ በጽሑፍ የወጣውን ድንጋጌ ቅጂ ሰጠው። ቅጂውን ለአስቴር እንዲያሳያትና እንዲያስረዳት እንዲሁም ወደ ንጉሡ ገብታ ሞገስ እንዲያሳያት እንድትለምነውና ስለ ሕዝቧ በግንባር ቀርባ እንድትማጸነው ይነግራት ዘንድ+ አሳሰበው።