የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አስቴር 3:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ወጣት ሽማግሌ፣ ሕፃንም ሆነ ሴት ሳይባል አይሁዳውያን በጠቅላላ በአንድ ቀን ይኸውም አዳር+ በተባለው በ12ኛው ወር 13ኛ ቀን ላይ እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲደመሰሱና ንብረታቸው እንዲወረስ+ የሚያዝዙ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች አማካኝነት ወደ ንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ ተላኩ።

  • አስቴር 9:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 አዳር* በተባለው በ12ኛው ወር፣ 13ኛ ቀን፣+ የንጉሡ ቃልና ሕግ በሚፈጸምበት+ እንዲሁም የአይሁዳውያን ጠላቶች በአይሁዳውያን ላይ ድል እንደሚቀዳጁ ተስፋ አድርገው በነበረበት ቀን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነ፤ አይሁዳውያኑ የሚጠሏቸውን ሰዎች ድል አደረጉ።+ 2 አይሁዳውያኑ እነሱን ለመጉዳት በሚሹ ሰዎች ላይ እጃቸውን ለማንሳት በንጉሥ አሐሽዌሮስ+ አውራጃዎች በሙሉ በሚገኙ ከተሞቻቸው ውስጥ ተሰባሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርቷቸው ስለነበር ሊቃወማቸው የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+

  • አስቴር 9:16, 17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩት የቀሩት አይሁዳውያንም ተሰብስበው ሕይወታቸውን ከጥቃት ተከላከሉ።*+ እነሱን ይጠሏቸው ከነበሩት ሰዎች መካከል 75,000 ሰዎችን በመግደል ጠላቶቻቸውን አጠፉ፤+ ይሁንና አንድም ምርኮ አልወሰዱም። 17 ይህ የሆነው አዳር በተባለው ወር 13ኛ ቀን ላይ ነበር፤ እነሱም በ14ኛው ቀን አረፉ፤ ዕለቱንም የግብዣና የሐሴት ቀን አደረጉት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ