-
አስቴር 8:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 በንጉሡ ስም የተጻፈንና በንጉሡ የማኅተም ቀለበት የታተመን ድንጋጌ መሻር ስለማይቻል አይሁዳውያንን በተመለከተ ተገቢ መስሎ የታያችሁን ማንኛውንም ነገር በንጉሡ ስም ጻፉ፤ በንጉሡም የማኅተም ቀለበት አትሙት።”+
-
-
ዳንኤል 6:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ከዚያም ድንጋይ አምጥተው በጉድጓዱ አፍ* ላይ ገጠሙት፤ ንጉሡም በዳንኤል ላይ የተወሰደው እርምጃ እንዳይለወጥ፣ በራሱ የማኅተም ቀለበትና በመኳንንቱ የማኅተም ቀለበት በድንጋዩ ላይ አተመበት።
-