-
አስቴር 3:8-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ከዚያም ሃማ ንጉሥ አሐሽዌሮስን እንዲህ አለው፦ “በግዛትህ ውስጥ ባሉት አውራጃዎች ሁሉ+ ተበታትኖና ተሰራጭቶ የሚገኝ፣+ የሚመራበትም ሕግ ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ የተለየ አንድ ሕዝብ አለ፤ የንጉሡንም ሕጎች አያከብርም፤ ንጉሡም ይህን ሕዝብ ዝም ብሎ መመልከቱ ይጎዳዋል። 9 ለንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው እነዚህ ሰዎች እንዲጠፉ የሚያዝዝ ድንጋጌ በጽሑፍ ይውጣ። እኔም ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት እንዲያስገቡ ለባለሥልጣናቱ 10,000 የብር ታላንት* እከፍላለሁ።”*
10 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የማኅተም ቀለበቱን ከእጁ አውልቆ+ የአይሁዳውያን ጠላት ለነበረው ለአጋጋዊው+ ለሃመዳታ ልጅ ለሃማ ሰጠው።+ 11 ንጉሡም ሃማን “ተገቢ መስሎ የታየህን እንድታደርግበት ብሩም ሆነ ሕዝቡ ለአንተ ተሰጥቷል” አለው።
-