-
አስቴር 3:2-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 በንጉሡ በር የነበሩት የንጉሡ አገልጋዮች በሙሉ ሃማን እጅ ይነሱትና ለእሱ ይሰግዱለት ነበር፤ ንጉሡ እንዲህ እንዲደረግለት አዝዞ ነበርና። መርዶክዮስ ግን እጅ ለመንሳትም ሆነ ለመስገድ ፈቃደኛ አልሆነም። 3 በመሆኑም በንጉሡ በር የነበሩት የንጉሡ አገልጋዮች መርዶክዮስን “የንጉሡን ትእዛዝ የማታከብረው ለምንድን ነው?” አሉት። 4 በየቀኑ ይህን ጉዳይ ቢያነሱበትም እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም የመርዶክዮስ አድራጎት በቸልታ የሚታለፍ እንደሆነና+ እንዳልሆነ ለማየት ጉዳዩን ለሃማ ነገሩት፤ መርዶክዮስ አይሁዳዊ መሆኑን ነግሯቸው ነበርና።+
5 ሃማም መርዶክዮስ እሱን እጅ ለመንሳትና ለእሱ ለመስገድ ፈቃደኛ አለመሆኑን ባስተዋለ ጊዜ እጅግ ተቆጣ።+
-