ዘፍጥረት 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+ መዝሙር 49:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በሚሞትበት ጊዜ ከእሱ ጋር አንዳች ነገር ሊወስድ አይችልምና፤+ክብሩም አብሮት አይወርድም።+ መክብብ 5:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ሰው ከእናቱ ማህፀን ራቁቱን እንደወጣ ሁሉ፣ ልክ እንደዚያው ተመልሶ ይሄዳል።+ ደግሞም ከደከመበት ነገር ሁሉ ሊወስደው የሚችል አንዳች ነገር የለም።+ መክብብ 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤+ መንፈስም* ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል።+ 1 ጢሞቴዎስ 6:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለምና፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም።+