ዳንኤል 12:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 “አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ። ታርፋለህ፤ ሆኖም በዘመኑ ፍጻሜ ዕጣ ፋንታህን ለመቀበል* ትነሳለህ።”+ ዮሐንስ 5:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+ ዮሐንስ 11:43, 44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ።+ 44 የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው።
28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+
43 ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ።+ 44 የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው።