መዝሙር 55:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ። ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑምእንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+ ምሳሌ 12:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጥበበኞች ምላስ ግን ፈውስ ነው።+