ኢዮብ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ኢዮብም ገላውን የሚያክበት ገል ወሰደ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ።+ ኢዮብ 2:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚያም ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት መሬት ላይ ከእሱ ጋር ተቀመጡ። ሥቃዩ በጣም ከባድ+ መሆኑን ስለተረዱ ከመካከላቸው አንድም ቃል የተናገረው አልነበረም። ኢዮብ 7:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በተኛሁ ጊዜ ‘የምነሳው መቼ ነው?’ እላለሁ።+ ሌሊቱም ሲረዝም ጎህ እስኪቀድ* ድረስ ያለእረፍት እገላበጣለሁ።