-
ኢዮብ 20:26-29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 ውድ ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ይዳረጋል፤
ማንም ያላርገበገበው እሳት እሱን ይበላዋል፤
በድንኳኑ ውስጥ የቀረ ማንኛውም ሰው ጥፋት ይደርስበታል።
27 ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፤
ምድር በእሱ ላይ ትነሳለች።
28 ጎርፍ ቤቱን ጠርጎ ይወስደዋል፤
በአምላክ የቁጣ ቀን* የውኃ መጥለቅለቅ ይከሰታል።
29 ክፉ ሰው ከአምላክ የሚቀበለው ድርሻ፣
አምላክም የወሰነለት ርስት ይህ ነው።”
-