ኢዮብ 19:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የገዛ ወንድሞቼን ከእኔ አራቀ፤የሚያውቁኝም ሰዎች ጥለውኝ ሄዱ።+ ኢዮብ 19:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤+የምወዳቸውም ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ።+ መዝሙር 31:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ባላጋራዎቼ ሁሉ፣በተለይ ደግሞ ጎረቤቶቼ ተሳለቁብኝ።+ የሚያውቁኝ ሰዎችም እጅግ ፈሩኝ፤በአደባባይ ሲያዩኝ ከእኔ ይሸሻሉ።+ መዝሙር 142:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ቀኝ እጄን ተመልከት፤ስለ እኔ ግድ የሚሰጠው* ሰው እንደሌለ እይ።+ ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም፤+ስለ እኔ* የሚያስብ ማንም የለም።