1 ሳሙኤል 12:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ይሖዋ ስለ ታላቁ ስሙ ሲል+ ሕዝቡን አይተውም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ እናንተን የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ፈልጓል።+ መዝሙር 37:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም።+ ע [አይን] ምንጊዜም ጥበቃ ያገኛሉ፤+የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።+ ዕብራውያን 13:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤+ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ።+ እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና።+