ዘፀአት 15:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 እንዲህም አላቸው፦ “የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል በጥንቃቄ ብታዳምጡ፣ በእሱ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርጉ፣ ለትእዛዛቱ ጆሯችሁን ብትሰጡና ሥርዓቶቹን በሙሉ ብታከብሩ+ በግብፃውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤+ ምክንያቱም እኔ ይሖዋ እፈውሳችኋለሁ።”+ መዝሙር 41:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤+በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ። መዝሙር 147:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል፤ቁስላቸውን ይፈውሳል። ኢሳይያስ 33:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በዚያም የሚቀመጥ* ማንኛውም ሰው “ታምሜአለሁ” አይልም።+ በምድሪቱ ላይ የሚቀመጡ በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።+ ያዕቆብ 5:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን* ሰው ይፈውሰዋል፤ ይሖዋም* ያስነሳዋል። በተጨማሪም ኃጢአት ሠርቶ ከሆነ ይቅር ይባላል። ራእይ 21:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤*+ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤+ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።+ ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”
26 እንዲህም አላቸው፦ “የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል በጥንቃቄ ብታዳምጡ፣ በእሱ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርጉ፣ ለትእዛዛቱ ጆሯችሁን ብትሰጡና ሥርዓቶቹን በሙሉ ብታከብሩ+ በግብፃውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤+ ምክንያቱም እኔ ይሖዋ እፈውሳችኋለሁ።”+
4 እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤*+ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤+ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።+ ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”