መዝሙር 78:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 እሱ ግን መሐሪ ነው፤+በደላቸውን ይቅር ይል* ነበር፤ ደግሞም አላጠፋቸውም።+ ቁጣውን ሁሉ ከመቀስቀስ ይልቅብዙ ጊዜ ስሜቱን ይገታ ነበር።+ ኢሳይያስ 49:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለች?ከማህፀኗ ለወጣውስ ልጅ አትራራም? እነዚህ ሴቶች ቢረሱ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልረሳሽም።+ ሚልክያስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “የእኔ ልዩ ንብረት*+ በማደርጋቸውም ቀን እነሱ የእኔ ይሆናሉ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “አባት ለሚታዘዝለት ልጁ እንደሚራራ እኔም እራራላቸዋለሁ።+ ያዕቆብ 5:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን* ሰው ይፈውሰዋል፤ ይሖዋም* ያስነሳዋል። በተጨማሪም ኃጢአት ሠርቶ ከሆነ ይቅር ይባላል።