መዝሙር 77:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በሥራዎችህም ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤ያከናወንካቸውንም ነገሮች አውጠነጥናለሁ።+ መዝሙር 143:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።* ኤርምያስ 9:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦ ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ።
24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦ ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ።