መዝሙር 68:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለአምላክ ዘምሩ፤ ለስሙም የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+ በበረሃማ ሜዳዎች* እየጋለበ ለሚያቋርጠው ለእሱ ዘምሩ። ስሙ ያህ* ነው!+ በፊቱ እጅግ ደስ ይበላችሁ! መዝሙር 113:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 113 ያህን አወድሱ!* እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤የይሖዋን ስም አወድሱ። ራእይ 19:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከዚህ በኋላ በሰማይ እንደ ብዙ ሠራዊት ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅ ሰማሁ። እንዲህም አሉ፦ “ያህን አወድሱ!*+ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው፤