ሉቃስ 12:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያም “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም፤+ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም* ሁሉ ተጠበቁ”+ አላቸው። 1 ጢሞቴዎስ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነውና፤ አንዳንዶች በዚህ ፍቅር ተሸንፈው ከእምነት ጎዳና ስተው ወጥተዋል፤ እንዲሁም ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።+ ዕብራውያን 13:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤+ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ።+ እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና።+
10 የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነውና፤ አንዳንዶች በዚህ ፍቅር ተሸንፈው ከእምነት ጎዳና ስተው ወጥተዋል፤ እንዲሁም ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።+