2 ነገሥት 10:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከዚያም “አብረኸኝ ሂድና ይሖዋን የሚቀናቀንን ማንኛውንም ነገር እንደማልታገሥ* እይ”+ አለው። እነሱም በጦር ሠረገላው አብሮት እንዲሄድ አደረጉ። መዝሙር 69:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል፤+ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋም በእኔ ላይ ደረሰ።+ ዮሐንስ 2:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ደቀ መዛሙርቱም “ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት ይበላኛል”+ ተብሎ የተጻፈው ትዝ አላቸው።