መክብብ 9:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤+ ሙታን ግን ምንም አያውቁም፤+ ከእንግዲህም የሚያገኙት ብድራት* የለም፤ ምክንያቱም የሚታወሱበት ነገር ሁሉ ተረስቷል።+ መክብብ 9:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር* ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።+ ኢሳይያስ 38:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 መቃብር* ከፍ ከፍ ሊያደርግህ አይችልምና፤+ሞትም ሊያወድስህ አይችልም።+ ወደ ጉድጓድ የሚወርዱ በታማኝነትህ ተስፋ ሊያደርጉ አይችሉም።+