መዝሙር 16:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 የሕይወትን መንገድ አሳወቅከኝ።+ በፊትህ* ብዙ ደስታ አለ፤+በቀኝህ ለዘላለም ደስታ* አለ። መዝሙር 45:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ጽድቅን ወደድክ፤+ ክፋትን ጠላህ።+ ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት+ ቀባህ።+