ዘዳግም 32:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ምክንያቱም ቁጣዬ እሳት አቀጣጥሏል፤+እሱም እስከ መቃብር* ጥልቀት ድረስ ዘልቆ ይነድዳል፤+ምድርንና ምርቷን ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቃጥላል። መዝሙር 110:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤+በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።+ ሚልክያስ 4:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤+ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።
4 “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤+ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።