ሉቃስ 22:44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 ሆኖም በከፍተኛ ጭንቀት ተውጦ ከበፊቱ ይበልጥ አጥብቆ መጸለዩን ቀጠለ፤+ ላቡም መሬት ላይ እንደሚንጠባጠብ ደም ሆኖ ነበር። ዮሐንስ 12:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 አሁን ተጨንቄአለሁ፤*+ እንግዲህ ምን ማለት እችላለሁ? አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ።+ ይሁንና የመጣሁት ለዚህ ሰዓት ነው።