መዝሙር 18:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ይሖዋ እንደ ጽድቄ ወሮታ ይከፍለኛል፤+እንደ እጄ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኛል።+ መዝሙር 26:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እኔ ግን ንጹሕ አቋሜን ጠብቄ እመላለሳለሁ። ታደገኝ፤* ሞገስም አሳየኝ። መዝሙር 41:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 እኔ በበኩሌ ንጹሕ አቋሜን* በመጠበቄ ትደግፈኛለህ፤+በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።+