ዘዳግም 15:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* መዝሙር 112:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በብዛት* አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ።+ צ [ጻዴ] ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል።+ ק [ኮፍ] የገዛ ብርታቱ* በክብር ከፍ ከፍ ይላል። ምሳሌ 14:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ባልንጀራውን የሚንቅ ኃጢአት ይሆንበታል፤ለችግረኞች የሚራራ ግን ደስተኛ ነው።+ ምሳሌ 22:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ለጋስ ሰው* ይባረካል፤ምግቡን ለድሃ ያካፍላልና።+
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።*