ማቴዎስ 21:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “እነዚህ የሚሉትን ትሰማለህ?” አሉት። ኢየሱስም “አዎ እሰማለሁ። ‘ከልጆችና ከሕፃናት አፍ ምስጋና አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁም?” አላቸው።+ ሉቃስ 10:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች+ ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ። አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና።+ 1 ቆሮንቶስ 1:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤+
21 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች+ ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ። አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና።+