የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 1:16-21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ከዚያም ቤርሳቤህ በንጉሡ ፊት ተደፍታ ሰገደች፤ ንጉሡም “ጥያቄሽ ምንድን ነው?” አላት። 17 እሷም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ‘ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል፤ በዙፋኔም ላይ የሚቀመጠው እሱ ነው’ በማለት ለአገልጋይህ በአምላክህ በይሖዋ የማልክላት አንተ ነበርክ።+ 18 ይኸው አሁን ግን አዶንያስ ንጉሥ ሆኗል፤ ጌታዬ ንጉሡም ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።+ 19 እሱም በጣም ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ እንስሳትንና በጎችን መሥዋዕት አድርጓል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ ካህኑን አብያታርንና የሠራዊቱን አለቃ ኢዮዓብን ጠርቷል፤+ አገልጋይህን ሰለሞንን ግን አልጠራውም።+ 20 አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እስራኤላውያን በሙሉ ከጌታዬ ከንጉሡ በኋላ በዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ እንድታሳውቃቸው ዓይኖቻቸው አንተ ላይ ናቸው። 21 አለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰለሞን እንደ ከዳተኞች ተደርገን እንቆጠራለን።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ