14 “የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ።+
ዛሬ ስእለቴን ፈጽሜአለሁ።
15 አንተን ለማግኘት የወጣሁት ለዚህ ነው፤
አንተን ፍለጋ ወጣሁ፤ ደግሞም አገኘሁህ!
16 መኝታዬን ባማረ የአልጋ ልብስ፣
ከግብፅ በመጣ በቀለማት ያሸበረቀ በፍታ አስጊጬዋለሁ።+
17 አልጋዬ ላይ ከርቤ፣ እሬትና ቀረፋ አርከፍክፌአለሁ።+
18 ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤
እርስ በርሳችን ፍቅራችንን በመግለጽ እንደሰት፤
19 ባሌ ቤት የለምና፤
ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል።
20 በከረጢት ገንዘብ ይዟል፤
ደግሞም ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን ድረስ ወደ ቤት አይመለስም።”
21 እንደ ምንም ብላ አግባብታ ታሳስተዋለች።+
በለሰለሰ አንደበቷ ታታልለዋለች።