ዘፍጥረት 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከዚያ በኋላ ቃየን ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳው ላይ ሳሉም ቃየን ወንድሙን አቤልን ደብድቦ ገደለው።+ ዘፍጥረት 4:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? ስማ! የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው።+ ዘኁልቁ 35:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ሞት ለሚገባው ነፍሰ ገዳይ ሕይወት* ቤዛ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።+ ዘዳግም 27:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “‘ንጹሑን ሰው* ለመግደል ሲል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)